Bole Addis Secondary School
Announcement የቦሌ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ራዕይ፣ ተልኮ፣ዓላማ እና እሴቶች

የቦሌ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ራዕይ፣ ተልኮ፣ዓላማ እና እሴቶች

29th January, 2025

ቦሌ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 

 ራዕይ፣ ተልኮ፣ዓላማ እና

እሴቶች

ራዕይ

በት/ቤታችን ውጤታማ የትምህርት ሥርዓት በማስፈን በ2020 ዓ.ም ሃገር አቀፋዊ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በልማት' በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ እና ስነ ምግባር

ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የተሟላ ስብዕና ያላቸው ዜጎችን ማፍራት፡፡


ተልዕኮ

የቦሌ አዲስ 2ኛ ደ/ት/ቤት በአካባቢዉ የሚገኙ ነዋሪዎች በትምህርት ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ ለትምህርት መዋቅሩና በትምህርት መስክ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍ በመስጠት፣ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር፤ የትምህርት ፍትሓዊነትን በማስፋፋት የት/ ቤቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ፤ሃገር አቀፋዊ ደረጃዉን የጠበቀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት በተስማሚ ፕሮግራሞች ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ማድረስ፡፡


ዓላማ

በቦሌ አዲስ 2ኛ ደ/ት/ቤት የትምህርት ጥራቱን፣ ሽፋኑን፣ ፍትሐዊነቱን፣ ተገቢነቱንና ብቃቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ ተግባራዊ በማድርግ በሁለንተናዊ ስብዕና የታነጸ ትውልድ በመፍጠር ለት/ቤቱ ብሎም ለክ/ከተማው አስተዳደር ዘላቂ ልማት ተገቢውን አስተዋጽኦ ማድረግ፡፡


እሴቶች

·         ግልጽነት

·         ተጠያቂነት

·         በእውቀትና በእምነት መምራት

·         የላቀ አገልግሎት መስጠት

·         ለለውጥ ዝግጁነት

·         ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ መስጠት

·         በመልካም ስነምግባር የታነጹ ዜጎችን ማፍራት

·         በጥናትና ምርምር የትምህርት ችግሮችን መፍታት

·         በጋራ መስራት

·         ውጤታማነት


                  ትምህርት ለህብረተሰብ ሁለንተናዊ እድገት መሰረት ነው!


.

Copyright © All rights reserved.

Created with