ቦሌ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የት/ቤቱ አመሰራረት
ቦሌ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር ከተከፈቱ የመንግስት አዳዲስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ይፋዊ የማስተማር ስራውንም ከጥቅምት 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ 841 የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል ጀምሯል፡፡
በ2017 ዓ.ም በአጠቃላይ 1,262 ተማሪዎችን በ9ኛ፣10ኛ፣11ኛ እና 12ኛ ክፍል መደበኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር-ማስተማር ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የመምህራን ብዛት በተመለከተ 72 መምህራንን ያሉት ሲሆን ሁሉንም መምህራን በመማር- ማስተማር ሂደት በማሳተፍ የት/ት ስራውን በሙሉ ቀን ት/ት ክፍለ ጊዜ እየተገበረ ይገኛል፡፡
ትምህርት ለህብረተሰብ
ሁለንተናዊ እድገት መሰረት ነው!